ስለ

የማርያም ማዕድ ማኅበር

ማኅበራችን ከምስረታ እስከዛሬ

የማርያም ማዕድ ማኅበር በ2015 ሚያዝያ ወር በአራት በጎ አድራጊዎች እና በሶስት ድጋፍ ፈላጊ ወንድም እና እህቶች ተጀመረ ። የማኅበራችን የአባላት ቁጥር በ7 ወራት ውስጥ (ከሚያዝያ 2015 እስከ ኅዳር 30 2016) ከ 4 ወደ 84 አድጓል። የገንዘብ መዋጮ የማኅበራችን ወርሃዊ የገንዘብ ወርሃዊ መዋጮ ባለፉት 5 ወራት ውስጥ ከ 5000.0 ወደ 84,850.00 የኢትዮጵያ ብር አድጓል። የማርያም ማዕድ ማኅበር አገልግሎቶች በሚያዝያ 2015 ወር በሽንቁሩ ደብረ መድሐኒት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን የተጀመረ ሲሆን በሐምሌ 2015 ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ገዳምን፤ እንዲሁም በጥቅምት 2016 በአክሱም ፅዮን ርዕሰ አድባራት ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ፅዮን ቤተ ክርስትያንን፣ አካትቶ በሶስት ስፍራዎች ይሰጣል። በመሆኑም በአሁኑ ውቅት፦ በሽንቁሩ ደብረ መድሐኒት ቅዱስ ሚካኤል ለአርባ ተጠቃሚዎች በማርያም ማዕድ ቤት በየቀኑ ነጻ የበሰለ ምግብ ያቀርባል። በደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ገዳም የምግብ ባንክ በመክፈት አራት ኪሎ የበሶ ዱቈትና ሁለት ኪሎ ስኳር በነጻ ለሀምሳ ተጠቃሚዎቸ በየወሩ ያቀርባል። በአክሱም ፅዮን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ፅዮን ቤተ ክርስትያን ከሕዳር 11 2016 ጀምሮ በአክሱም ፅዮን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ፅዮን ቤተ ክርስትያን ለሀያ ገዳማውያን በየቀኑ ነጻ የበሰለ ምግብ ያቀርባል።

የማርያም ማዕድ ማኅበር
የአገልግሎት ዓይነቶች

የማርያም ማዕድ ማኅበር ስድስት ዓላማዎች ያሉት ሲሆን እነዚህም በአጭር እና በረጅም ጊዜ ዕቅድ የሚተገበሩ ናቸው፤ እነዚህም፦

የምግብ ምርት እና አገልግሎት

በአጭር ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ማዕድ ቤት›› በመባል የሚጠሩ የነጻ ምግብ ማዕከላትን በማቋቋም የምግብ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሁሉ የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ድጋፍ ማድረግ፤ ‹‹የማርያም ማዕድ የምግብ ባንክ›› በመባል የሚጠሩ የነጻ የምግብ ባንኮችን በማቋቋም የምግብ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሁሉ የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ነጻ የምግብ ድጋፍ ማድረግ፤ ‹‹የማርያም ማዕድ የምግብ መደብር›› በመባል የሚጠሩና የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን ለገበያ በማቅረብ የሚያስገኙት ትርፍ ለማኅበሩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የምግብ መደብሮችን ማቋቋም፣ እና የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ማስተዳደር፤

በረጅም ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ማዕድ ማኅበር የምግብ ማደራጃና ማቀነባበሪያ ድርጅት›› በመባል የሚጠራ እና የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ማኅበሩ ለሚያቋቁማቸው የማርያም ማዕድ ቤቶች፣ የማርያም ማዕድ የምግብ ባንኮች፣ እና ለማርያም ማዕድ የምግብ መደብሮች ለሽያጭ በማቅረብ ትርፉ ለማኅበሩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የማኅበሩን አቅም የሚያጎለብት የምግብ ማቀነባበሪያ ድርጅት ማቋቋም እና ማስተዳደር።

በአጭር ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ማዕድ ቤት›› በመባል የሚጠሩ የነጻ የመጠጥ ማዕከላትን በማቋቋም የመጠጥ ማለትም የንጹህ መጠጥ ውኃ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ ሌሎች የመጠጥ አይነቶችን ድጋፍ ለሚፈልጉ ሁሉ የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ድጋፍ ማድረግ፤ ‹‹የማርያም ማዕድ የመጠጥ ባንክ›› በመባል የሚጠሩ የነጻ የመጠጥ ማለትም የንጹህ መጠጥ ውኃ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ ሌሎች የመጠጥ ባንኮችን በማቋቋም የመጠጥ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሁሉ የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ነጻ የመጠጥ ድጋፍ ማድረግ፤ ‹‹የማርያም ማዕድ የንጹህ መጠጥ ውኃ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ የመጠጥ መደብር›› በመባል የሚጠሩና የተለያዩ የንጹህ መጠጥ ውኃ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ የመጠጥ ግብዓቶችን ለገበያ በማቅረብ የሚያስገኙት ትርፍ ለማኅበሩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የመጠጥ መደብሮችን ማቋቋም፣ እና የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ማስተዳደር፤

በረጅም ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ማዕድ የንጹህ መጠጥ ውኃ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ የመጠጥ ማደራጃና ማቀነባበሪያ ድርጅት›› በመባል የሚጠራ እና የተለያዩ የመጠጥ ግብዓቶችን በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ማኅበሩ ለሚያቋቁማቸው የማርያም ማዕድ ቤቶች፣ የማርያም ማዕድ የመጠጥ ባንኮች፣ እና የማርያም ማዕድ የንጹህ መጠጥ ውኃ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ የመጠጥ መደብሮች ለሽያጭ በማቅረብ ትርፉ ለማኅበሩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የማኅበሩን አቅም የሚያጎለብት የምግብ ማቀነባበሪያ ድርጅት ማቋቋም እና ማስተዳደር።

የመጠጥ ምርት እና አገልግሎት

የመጠለያ ግንባታ እና አገልግሎት

በአጭር ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ቤት›› በመባል የሚጠሩ ለእንግዳ ማረፊያ የሚሆኑ መጠለያዎችን መጠለያ ለሌላቸው ወንድሞች እና እህቶች መገንባት እና ማስተዳደር፤

በረጅም ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ማዕድ የኤንጂነሪንግ እና የግንባታ ድርጅት›› በመባል የሚጠራ እና የማርያም ቤቶችን በተመሳሳይም የመጠለያ ችግር ላለባቸው ወንድሞች እና እህቶች እንደ ፍላጎታቸው የመጠለያ ቤቶችን በነጻ የሚገነባ እንዲሁም ትርፉ ለማኅበሩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የተለያዩ የኤንጂነሪንግ ግብዓቶችን / ውጤቶችን የሚያቀርብና ግንባታዎችን የሚያከናውን ተቋም ማቋቋም እና ማስተዳደር።

በአጭር ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ማዕድ አልባሳት እና መጫምያ ባንክ›› በመባል የሚጠሩ የነጻ አልባሳት እና መጫምያ ባንኮችን በማቋቋም የአልባሳት እና የመጫምያ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሁሉ የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ድጋፍ ማድረግ፤ ‹‹የማርያም ማዕድ አልባሳት እና መጫምያ መደብር›› በመባል የሚጠሩና የተለያዩ አልባሳትን እና መጫምያዎችን ለገበያ በማቅረብ የሚያስገኙት ትርፍ ለማኅበሩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል መደብሮችን ማቋቋም፣ እና የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ማስተዳደር፤

በረጅም ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ማዕድ አልባሳት እና መጫምያ ማምረቻ ድርጅት ›› በመባል የሚጠራና የተለያዩ አልባሳት እና መጫሚያዎችን በማምረትና ለሽያጭ በማቅረብ ትርፉ ለማኅበሩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የማኅበሩን አቅም የሚያጎለብት አልባሳት እና መጫምያ ማምረቻ ድርጅት ማቋቋም እና ማስተዳደር።

አልባሳት እና መጫምያ ምርት እና አገልግሎት

የጤና አጠባበቅ ግብዓቶች ምርት እና አገልግሎት በአጭር ጊዜ ዕቅድ

በአጭር ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ማዕድ የመጀመሪያ ደረጃ ክሊኒክ / መካከለኛ ክሊኒክ / ከፍተኛ ክሊኒክ / ሆስፒታል / ጠቅላላ ሆስፒታል / ሪፈራል ሆስፒታል›› በመባል የሚጠሩ የነጻ የሕክምና ማዕከላትን በማቋቋም ነጻ የጤና ድጋፍ ለሚፈልጉ ሁሉ የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ የጤና ድጋፍ ማድረግ፤ ‹‹የማርያም ማዕድ ነጻ የመድሐኒት ባንክ›› በመባል የሚጠሩና የመድሐኒት ድጋፍ ለሚፈልጉ ሁሉ የጤና አገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ነጻ የመድሐኒት ድጋፍ ማድረግ፤ እና ‹‹የማርያም ማዕድ የባዮሜዲካል ኤንጂነሪንግ እና የመድሐኒት መደብር›› በመባል የሚጠራና የተለያዩ የጤና አጠባበቅ ግብዓቶችን እና መድሐኒቶችን ለገበያ በማቅረብ የሚያስገኘው ትርፍ ለማኅበሩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የባዮሜዲካል ኤንጂነሪንግ እና የመድሐኒት መደብርን ማቋቋም፣ እና የአገልግሎት ጥራትን ባረጋገጠ ሁኔታ ማስተዳደር፤

በረጅም ጊዜ ዕቅድ

‹‹የማርያም ማዕድ የባዮሜዲካል ኤንጂነሪንግ እና የመድሐኒት ማምርቻ ድርጅት›› በመባል የሚጠራና የተለያዩ የባዮሜዲካል ኤንጂነሪንግ ውጤቶችን እና መድሐኒቶችን በማምረት ትርፉ ለማኅበሩ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የተለያዩ የጤና አጠባበቅ ግብዓቶችን እና መድሐኒቶችን የሚያመርት ተቋም ማቋቋም እና ማስተዳደር።

Scroll to Top